የአዲስ ከተማ አስተዳደር ህንጻ 5ኛ ወለል
+251923309794
ማስታወቂያ
ዓርብ, ህዳር 14, 2016 ዓ.ም
መግቢያ
ስለ እኛ
የጽ/ቤቱ ራዕይ ፣ ተልዕኮና እሴቶች
የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት
የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
ተቋማዊ አደረጃጀት
የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች
የዜጎች የስምምነት ሰነድ
ደንብና መመሪያዎች
ማስታወቂያ
የደንበኞች አገልግሎት
አገልግሎቶች
የፕሮጀክት ጥናትና ዲዛይን ዝግጅት ቡድን
የምህንድስና ግዥ ቡድን
የኮንትራት አስተዳደር ቡድን
የመንግስት ኮንስትራክሽን ኦዲት ቡድን
ለመልካም አስተዳደር አስተያየት
የቅሬታ አስተያየት መስጫ
የአገልግሎት እርካታ አስተያየት መስጫ
የጽ/ቤቱን ሮቦት ይጠይቁ
ሚዲያ
ዜና | News
Online TV
Web App
መጽሄቶች | Magazines
Photographs
ፕሮጀክት
ይግቡ
መግቢያ
ስለ እኛ
የጽ/ቤቱ ራዕይ ፣ ተልዕኮና እሴቶች
የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት
የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
የዜጎች የስምምነት ሰነድ
አገልግሎቶች
ተቋማዊ አደረጃጀት
ሚዲያ
ዜናዎች | News
መጽሄቶች | Magazine
Online TV
ጠቃሚ መረጃዎች
ደንብና መመሪያዎች
ብሮሸር
የደንበኞች የእርካታ ዳሰሳ ገጽ
Web APP
ወረዳዎች
ወረዳ 1
ወረዳ 2
ወረዳ 3
ወረዳ 4
ወረዳ 5
ወረዳ 6
ወረዳ 7
ወረዳ 8
ወረዳ 9
ወረዳ 10
ይግቡ
ዜና | Oduu | News
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የዛሬ ሁለት ወር ያስጀመርነው የቅጠል ተራ የቤቶች ግንባታ በአስደናቂ ፍጥነት እየተሰራ ነው።
ሰኔ 17, 2018
ዛሬ የቤቶቹን ግንባታ ሂደት በሳይቱ በመገኘት የገመገምን ሲሆን፣ የዛሬ ሁለት ወር የተጀመሩ ህንጻዎች 9ኛ ወለል ላይ መድረሳቸውን ተመልክተናል። ቦታውን ከማጽዳት ጋር በተያያዘ የዛሬ ወር የተጀመሩ ህንጻዎችም 4ኛ እና 5ኛ ወለል ላይ የደረሱ ሲሆን ከሁለት ሳምንት በፊት የግንባታውን ሂደት ተመልክተን የጨመርናቸው ሶስት ህንጻዎችም ጅማሮ በጥሩ ሂደት ላይ ይገኛል። በፕሮጀክቶቹ የሚገነቡት መኖሪያ ቤቶች ብቻ ሳይሆኑ የንግድ፣ የጸጥታ፣ ትምህርት ቤት እና ጤና ተቋማት፣ የስፖርት ማዘዉተሪያ፣ የህፃናት መጫወቻ እና የመሳሰሉ ማህበራዊ አገልግሎት መስጫዎች እንዲሁም ሌሎች የህዝብ የጋራ መገልገያዎች እኩል ትኩረት ተሰጥቷቸዋል። በመሆኑም የምንገነባው መኖሪያ ቤት ብቻ ሳይሆን ህጻናት ቦርቀው የሚያድጉበት፣ ወጣቶች የአካል እና የአዕምሮ ብቃታቸውን የሚያዳብሩበት፣ ዜጎቻችን አገልግሎቶችን በቅርበት የሚገኙበት እና ክብራችንን የሚያስጠብቅ ምቹና ፅዱ አካባቢን ነው። በአጠቃላይ የቅጠል ተራ መኖሪያ መንደርን ትናንት ካስጀመርነው የገዳም ሰፈር እና በመሀሉ ላይ የሚገኘውን የጣልያን ሰፈር ጨምረን አገናኝተን በማልማት አካባቢውን የዘመነ አኗኗርና ሰፊ የስራ እድል የሚፈጥር አካባቢ እናደርገዋለን። በምርጫ ወቅት ላይ ሆነን የፕሮጀክቶቹ ግንባታ ሳይቀዛቀዝ መቀጠሉ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ነዋሪዎቻችንን በታማኝነት የማገልገል አቋማችን ፅኑ መሆኑን ያሳያል። ህንጻዎቹን በጥራት እና በፍጥነት ገንብተው በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ እየሰሩ የሚገኙ አመራሮቻችንን፣ ሰራተኞቻችንን፣ ማህበራትን፣ ተቋራጮችን እና ሁሉንም ባለድርሻ አካላት አመሰግናለሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ! - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ዜና | Oduu | News
በጋራ ሆነን የአረንጓዴ አሻራን በማኖር ስራችን ሀገራችን ዘመን የማይሽረው ታሪክ አስቀምጣለች።
ሰኔ 16, 2018
ባለፉ ሰባት ዓመታት እንደሀገር በሁሉም ኢትዮጵያዊ ትብብር 48 ቢሊዮን ችግኝ በመትከል ታሪካዊ እና አስደማሚ አሻራ አኑረናል። በከተማችንም ባለፋት ሰባት ዓመታት 90 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል የአረንጓዴ ሽፋናችንን እጅግ ዝቅተኛ ከነበረበት 2 .8 በመቶ ወደ 24 በመቶ ማድረስ ችለናል። በአረንጓዴ አሻራ መረሃ ግብራችን የተራቆቱ አካባቢዎች አረንጓዴ ለብሰዋል፤ የነጠፉ ወንዞች እና አካባቢዎች ማንሰራራት ችለዋል። አዲስ አበባችንም ንፁህ፣ ውብ፣ ለመኖር ምቹ እና የቱሪስት ማዕከል መሆን ችላለች። የምንተክለው ተስፋን፣ ልማትን፣ ልምላሜን፣ ጥላን፣ ምግባችንን ብሎም ብልፅግናን ነው። የምንተክለዉ ለዛሬ ጥቅማችን ብቻ ሳይሆን ለትውልድ እዳን ሳይሆን የልምላሜና የብልፅግና ምንዳን ለማውረስ ነው ። ዛሬ በከተማችን 6 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ክቡር አቶ አገኘሁ ተሻገር በተገኙበት በበሻሌ ወንዝ ዳርቻ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሂደናል። ውድ የከተማችን ነዋሪዎች በወንዝ ዳርቻዎች፤ በጤና፣ ትምህርትና በሃይማኖት ተቋማት፤ በግል ሴክተሮች እና በጎዳናዎች ለምግብነት የሚውሉ አትክልት እና ፍራፍሬዎችን፣ የጥላ እና የውበት ዛፎችን በመትከል ከተማችን ውብ፣ ጽዱ ኢረንጓዴና ለኑሮ ምቹ ከተማ ለማድረግ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ህፃን አዋቂ ሳንል ሁሉም ዜጋ በጋራ በመሆን እንድናሳካው ጥሪዬን አስተላልፋለሁ። ችግኝ መትከል ብቻ በቂ አይደለም እንክብካቤን ይፈልጋል ። ስለሆነም የተከልናቸውን ችግኞች መከታተል፤ መንከባከብ ይኖርብናል። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ
መግቢያ
ስለ_እኛ
የጽ/ቤቱ ራዕይ ፣ ተልዕኮና እሴቶች
የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት
የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
አገልግሎቶች
ተቋማዊ አደረጃጀት
ሚዲያ
ዜናዎች | News
ፎቶግራፎች | Photo Gallery
ቪዲዮዎች | Videos
መግለጫዎች | Press Release
መጽሄቶች | Magazine
ጠቃሚ መረጃዎች
ደንብና መመሪያዎች
ብሮሸር
የደንበኞች የእርካታ ዳሰሳ ገጽ
Online TV
Web APP
የዛሬይቱ ልደታ
ወረዳዎች
ያግኙን
akdesign@gmail.com
+251923309794